Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከካርቱም አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረው አውሮፕላን ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ ምርመራ እያደረኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካርቱም አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረው የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ የበረራ አባላቱ ለጊዜው ከስራ መታገዳቸውን አስታወቀ፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ባሳለፍነው ሰኞ ከሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET343 አዲስ አበባ ካለው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር ያለው ግንኙነት ተቋረጦ እንደነበር የሚያመላክት መረጃ እንደደረሰው አስታውቋል፡፡
 
አውሮፕላኑ አዲስ አበባ ከሚገኘው አየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የነበረው ግንኙነት ከተስተካከለ በኋላም በሰላም ማረፉን ነው የገለጸው።
 
ከችግሩ ጋር ተያይዞም በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ የበረራ ሰራተኞች ለጊዜው ከስራ ታግደው ምርመራ እየተደረገ ነው ብሏል።
 
አየር መንገዱ በሚገኘው የምርመራ ውጤት መሰረት ተገቢውን እርምጃ እንደሚውስድም ነው ያስታወቀው።፡
 
የደንበኞችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ የዘወትር ቅድሚያ ተግባሩ መሆኑን ያወሳው አየር መንገዱ÷ይህን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.