Fana: At a Speed of Life!

አውሮፓውያን በአሜሪካ ምክንያት በረሃብ እና ብርድ እየተቀጡ ነው – ሩሲያ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋሺንግተን የአውሮፓ ኅብረትን ከሩሲያ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ ጫና በማድረግ ለረሃብ፣ ብርድ እና መገለል ዳርጋዋለች ሲሉ የሩሲያ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ ቪያቼስላቭ ቮሎዲን ገለጹ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ከሩሲያ ሲያገኝ የነበረውን የኃይል አቅርቦት እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት እንዲያቋርጥ ግፊት ያደረገችውም አሜሪካ ናት ብለዋል፡፡

በዚህ ምክንያት ቀጠናው ዓመታዊ የዋጋ ግሽበት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ አሻቅቧል ብለዋል ቪያቼዝላቭ ቮሎዲን፡፡

ቮሎዲን አስተያየት የሰጡት የአውሮፓ ኅብረት በዓለም አቀፍ የዋጋ ንረት ምክንያት በኃይል እጥረት ቀውስ መናጡን ተከትሎ ነው፡፡

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ኅብረቱ ቀውሱን ለመቅረፍ የአባል ሀገራቱን የጋዝ ፍጆታ በ15 በመቶ መቀነስ የሚያስችል ረቂቅ ዕቅድ ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የቀጠናውን የኃይል አቅርቦት ዕጥረት ያባባሰው ሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን ባላቋረጠችበት ሁኔታ ገና ለገና ልታቋርጥ ትችላለች በሚል ሥጋት ኅብረቱ ከወዲሁ መግዛት ለማቆም መወሰኑ ነው ተብሏል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ሩሲያ ለአውሮፓ ኅብረት የጋዝ አቅርቦት ልታቋርጥ ትችላለች የሚለውን ውንጀላ ውድቅ ማድረጋቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.