Fana: At a Speed of Life!

“የዋግ ላስታ ህዝቦች ታሪክና ለኢትዮጵያ ያበረከቱት አስተዋጽኦ “በሚል የፓናል ወይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት “የዋግ ላስታ ህዝቦች ታሪክና ለኢትዮጵያ ያበረከቱት አስተዋጽኦ “በሚል በሰቆጣ ከተማ የፓናል ወይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳር በሰቆጣ ከተማ የሻደይ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ጥናታዊ ጹሁፍ በፓናል ውይይት መልኩ መቅረብ ጀምሯል ።
በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ፣ የንግድ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ጀኔራሎችና የጦር መኮንኖች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈንታይቱ ካሴ ÷ በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግግር ማድረጋቸውን ከሰቆጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአገው ህዝቦች ታሪክ ፣ የዋግና ላስታ ህዝብ ለኢትዮጵያ ያበረከተው አስተዋጽኦ ፣ የተከአሳ ሃብት ምርት ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ፣ የዋግኽምራ እምቅ ሃብት ፣ የዋግ ማር ዕድሎች እና ችግሮች የሚሉ ጥናታዊ ጹሁፎች ቀርበው የጋራ መፍትሄ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.