Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ሻይ የጤና ጥቅሞች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)አረንጓዴ ሻይ መጠጣት የደም ሥኳር መጠንን መቆጣጠር ጨምሮ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት ጥናት አመላከተ፡፡

አረንጓዴ ሻይ ሰዎች በዓይነት 2 የሥኳር ሕመም እንዳይያዙ ቀድሞ ለመከላከል ብሎም የአንጀት እብጠትን ለማስታገስ እንደሚረዳም በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-አመጋገብ ፕሮፌሰር እና ከፍተኛ አጥኚ የሆኑት ዶክተር ሪቻርድ ብሩኖ በጥናታቸው ውጤት ጠቁመዋል፡፡

አረንጓዴ ሻይ አዕምሯችንን ከእርጅና ለመታደግ እና ተግባሩን በተሻለ እንዲከውን ለማገዝ ይረዳልም ተብሏል፡፡

አረንጓዴ ሻይ የካንሰር ሕመምን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችልም የኸልዝ ላይን መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም አረንጓዴ ሻይ ስትሮክን ጨምሮ ከልብ እና ከልብ ጡንቻዎች ጋር የተያያዙ ሕመሞችን ለመከላከል፣ ክብደት ለመቀነስ ፣ የደም ቅባት መጠን ለማስተካከል፣ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ፣ መጥፎ የአፍ ጠረንን ለማስወገድ፣ እንዲሁም የቆዳ እና የጉበት ጤናን ለመጠበቅም ሁነኛ መፍትሄ መሆኑም ተገልጿል፡፡

አረንጓዴ ሻይን በሻይነት ጥቅም ላይ ከማዋል በተጨማሪ በካፕሱል ፣ በፈሳሽ ወይም በዱቄት መልክ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.