Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ ሀገራዊ ስጋቶች ቀንሰዋል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች በወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ ሀገራዊ ስጋቶች መቀነሳቸውን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ተናገሩ፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ልማት ተመራማሪው ዶክተር መሀመድ አሊ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ሰላም በአንድ ወገን ብቻ የሚመጣ ባለመሆኑ በትብብር እና አብሮ በመቆም ሰላምን ማምጣት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በአንቦ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሴኔሳ ደምሴ እንዲሁ÷ ሰላም ሀገር ያሰበችበት ለመድረስ እና ብሔራዊ ጥቅሟን እንድታስከበር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ነው ያስደሩት፡፡

በህግ መስከበር እርምጃው የተገኘው አንጻራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገርም ህብረተሰቡ፣ መንግስት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅንጅት መስራት አለባቸው ነው ያሉት፡፡

ምሁራኑ መንግስት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እየወሰደ ያለው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ምሁራኑ አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይ የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድርግ እና ወደ ልማት ለመቀየርም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመንግስት ስር ሆነው የተለየ ዓላማ ያላቸው ሊኖሩ ስለሚችሉ፥ መንግስት የፖለቲካ እና የጸጥታ መዋቅሩን መፈተሽና የእርምት እርምጃ መውሰድ እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.