Fana: At a Speed of Life!

መጪውን የበዓል ግብይት የሚቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቋመ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪውን የበዓል ግብይት የሚቆጣጠር ከፌደራል መንግሥት፣ ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ ክልል ንግድቢሮዎች የተውጣጠ ግብረ ኃይል ተቋቋመ፡፡

ከመጪው የአዲስ ዓመት በዓል ጋር ተያይዞ የሚከሰት አላስፈላጊ የዋጋ ንረትን እንደሚቆጣጠር ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

መጪውን የበዓላት ጊዜ ግብይትና ስርጭት ለማሣለጥ ከፌደራል መንግሥት፣ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ እና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡

ግብረ ኃይሉ የተቋቋመው÷ ከበዓላት ጋር ተያይዞ የሚኖረውን የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች፣ የፋብሪካ ምርቶች፣ የአትክልትና የቁም እንስሣት እርድ ፍላጎት በበቂ አቅርቦት ለመሸፈን እንዲቻል እና አላስፈላጊ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ብሎም እርምጃ ለመውሰድ ነው ተብሏል።

ከግብረ ኃይሉ ጋር በተደረገው ውይይት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሠን መሐመድ እንደገለጹት÷ ከዚህ ቀደሞ መንግሥት የተለያዩ ምርቶችን በኅብረት ሽርክና ማኅበራት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ጨምሮ በተለያዩ የግብይት አማራጮች ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እያደረገ ነው፡፡

መጪው አዲስ ዓመት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለበዓላት ግብዓት የሚውሉ ምርቶችን እንዲሁም የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በበዓላት ወቅት የግብይት ስርአቱ ላይ የሚስተዋል አላስፈላጊ የዋጋ ንረትን መከታተልና መቆጣጠር እንደሚገባ ማሳሰባቸውን የንግድ ቀጣናዊ ሚኒስቴሩ ረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.