Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በ7 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የአነስተኛና መካከለኛ የኢንደስትሪ ፓርክ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በ7 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የአነስተኛና መካከለኛ የኢንደስትሪ ፓርክ ለመገንባት ስምምነት ተፈረመ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩ መልዕክት÷ ለአዲስ አበባ የመጀመርያና አዲስ ብስራት የሆነው የአነስተኛና መካከለኛ የኢንደስትሪ ፓርክ በ93 ሄክታር ላይ የሚገነባ ነው ብለዋል።

ስምምነቱን የከተማ አስተዳደሩ ከኤም ሲ ጂ እና ቲ ኤን ቲ ከተባሉ የኮንስትራክሽን ተቋራጮች ጋር ነው የተፈራረመው፡፡

በዛሬው እለት የተፈረመው የኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ ስምምነት፥ ለኢንደስትሪዎች መስፋፋት የሚያግዝ፣ ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን የሚያስቀርና በቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸው የላቁ፣ የስራ ባህላቸው የጎለበቱ፣ አምራች ዜጎችን የሚያፈራ እንደሚሆን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ከንቲባ ገልጸዋል፡፡

ግንባታው 21 የተለያየ ወለል ያላቸው የማኑፋክቸሪንግ ሼዶችና 400 የግብዓት አቅራቢዎችና ምርት መሸጫ ሱቆች ይኖሩታልም ነው ያሉት፡፡

ፓርኩ ከ18 እስከ 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል እንደሚፈጥርም ጠቅሰዋል፡፡

ከአግሮ ፕሮሰሲንግ ጀምሮ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የኮንስታራክሽን፣ የኬሚካል እና ፕላስቲክ፣ የኤሌክትሮኒክ፣ የመድሐኒት ማምረቻ እቃዎች ግብዓቶች የሚመረቱበት በመሆኑ በአጠቃላይ ለከተማችን ሁለንተናዊ ለውጥ አይነተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል ብለዋል።

“ኢትዮጵያ ወደ ምንመኝላት ብልፅግና እንድትጓዝ ኢንደስትሪን ማስፋፋት፣ የስራ ባህልን መቀየር፣ አምራቾችን ማበራከት፣ የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሽግግርን ማረጋገጥ የግድ ይለናል “ ነው ያሉት ከንቲባዋ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.