Fana: At a Speed of Life!

የሶለል በዓል በቆቦ ከተማ በድምቀት ተከበረ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶለል በዓል “ሶለልን በግንባር ለድልና ለነፃነት” በሚል መሪ መልዕክት በቆቦ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሰይድ አባተ በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሶለል በዓል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ባለፈው ዓመት ሳይከበር መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

የልጃገረዶች የነፃነትና የእኩልነት ቀን ማሳያ የሆነው ሶለል ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ስላለው ባህላዊ ይዘቱን እንደጠበቀ ለትውልድ ሊሻገር ይገባል ማለታቸውን የቆቦ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ለዚህ ደግሞ ይህ ትውልድ ኃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አካባቢው በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ሥር እንደነበር አስታውሰው÷ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎችና የተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የራያ ሕዝብ ባለው ገንዘብ እና ጉልበት በግንባታ ላይ ለሚገኘው የባህል ማዕከል አስተዋጽዖ ቢያበረክትም÷ አሸባሪው ህወሓት አካባቢውን በወረረበት ወቅት በመውደሙ የራያ ሕዝብ ማንነት መገለጫ የሆነውን የባህል ማዕከል ፕሮጀክት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መደበኛ በጀት ይዞ እንዲገነባው ጠይቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.