Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተሾመ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ፕሬዚዳንት እና በተቋሙ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሊ ሺንፈንግ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
 
አምባሳደር ተሾመ በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል ስለተከሰተው ጦርነትና የሰላም ድርድር ሂደት እንዲሁም ስለ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
 
አምባሳደሩ የሰሜኑ ግጭት መንግስት ተገዶ የገባበት መሆኑንና ከጅማሮው አንስቶ ጦርነቱን ለማስቀረት ከፍተኛና ተደጋጋሚ ጥረቶችን አድርጎ እንደነበርም አስረድተዋል።
 
ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላም መንግስት በጦርነቱ መሀል የተናጠል የተኩስ አቁም በማድረግ ለሰላም እድል ለመስጠት ከፍተኛ ስራ ሰርቷል ያሉት አምባሳደሩ÷ በቅርቡም መንግስት ያልተገደበ የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ በማሳለፍ የሰብዓዊ እርዳታ በየብስና በአየር እንዲደርስ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በዚህ ሁሉ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየችው ጠንካራ አጋርነትና እውነተኛ ወዳጅነት የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ አክብሮትና ምስጋና እንዳለውም አውስተዋል።
 
ፕሮፌሰር ሊ ሺንፈንግ በበኩላቸው÷ በሚዲያ ከሚሰሙት ይልቅ ከአምባሳደሩ በቀጥታ በአካል ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ለመስማትና ለመረዳት በመቻላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በቀጣይ ተቋማቸው ከኤምባሲው ጋር ያለውን ቅርብ ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውንም ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.