Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ በ500 ዓመታት ውስጥ የከፋ ድርቅ መከሰቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ በ500 ዓመታት ውስጥ የከፋ የተባለው ድርቅ መከሰቱን የአውሮፓ ህብረት ኤጀንሲ አስታወቋል፡፡

ህብረቱ በነሐሴ ወር ባወጣው ሪፖርት ÷ በድርቁ ምክንያት በተፈጠረው የአፈር እርጥበት መቀነስ 47 በመቶው የህብረቱ ክፍል የድርቅ አደጋ ስጋት እንደተደቀነበት አመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም 17 በመቶወቹ የድርቅ አደጋ አንዣቦባቸዋል ነው የተባለው።

ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በብዙ የአውሮፓ ግዛቶች የተከሰተው ከባድ ድርቅ እስከ ነሐሴ ወር መጀመሪያ ድረስ እየተባባሰ መምጣቱ ነው የተገለጸው ፡፡

የሜዲትራኒያን ባህርም እስከ ቀጣዩ ህዳር ወር ድረስ ሞቃታማ እና ደረቅ ሊሆን እንደሚችል በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በድርቁ ሳቢያ በርካታ ወንዞች እና ሐይቆች የውሃ መጠን መቀነስ እና መድረቅ እንዳጋጠማቸውም ኤጀንሲው አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም በባህር ትራንስፖርት መስተጓጎል ሲፈጥር፥ የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦትም በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ብሏል ኤጀንሲው።

በተጨማሪም በግርብርና ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋልም ነው ያለው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በተያዘው የፈረንጆቹ አመት የማሽላ ምርት ካለፉት አምስት አመታት አንጻር በ16 በመቶ፣ አኩሪ አተር በ15 በመቶ እንዲሁም የሱፍ ዘይት ምርቶች በ12 በመቶ እንደሚቀንሱ የአጄንሲው ትንበያ ያመላክታል።

በአውሮፓ የተከሰተው ድርቅ በ500 ዓመታት ውስጥ የከፋ መሆኑን መረጃችን በማጣቀስ የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን መግለጹን ሺንዋ እና ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.