ኢኮኖሚን ከውጭ ሀገራት ጥገኝነት ለማላቀቅ ቀጣይ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ስራዎች እንዳሉ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከውጭ ሀገራት ጥገኝነት ለማላቀቅ መንግስት እየሰራው ያለው ስራ መልካም ቢሆንም ቀጣይ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ስራዎች እንዳሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ግብርናውን ወደ ሰፋፊ ሜከናይዜሽን መቀየር፣ ኢንዱስትሪውን ማሳደግ እና የተሻለ ውጤት ሊገኝባቸው የሚችሉ ዘርፎች ላይ በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ በመስራት ማሻሻል እንደሚገባ ምሁራኑ ይገልጻሉ።
በአውሮፓ ህብረት የአደጋ ስጋት አመራር አማካሪው ጉቱ ቴሶ÷ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የተያዙትን እቅዶች እውን ለማድረግ ግብርናን ማዘመን ያስፈልጋል ብለዋል።
በዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህሩ አቶ ፋሲል ጣሰው÷ እሩቅ በማሰብ የትምህርት ዘርፉም ይህን ኢኮኖሚውን ከጥገኝነት የሚያላቅቅ እና ራስን በምግብ የመቻል ግቦችን የሚያግዝ መሆን እንደሚገባው አንስተዋል፡፡
በተለይ ፈጠራ እና የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ግኝት በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ትኩረት ሊሰጠው እና ሊበረታታ ይገባዋል ነው ያሉት፡፡
በትዕግስት አብርሃም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን