Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ጨረቃ ላይ ውሃ ማግኘት የሚያስችል የጨረር ቁስ ሰራ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው የናሳ ተመራማሪ ዶክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ቡልቻ ጨረቃ ላይ ውሃ ለማግኘት የሚያስችል በመጠን አነስተኛ የሆነ ቁስ የኳንተም ፊዚክስ ቀመርን በመጠቀም መስራቱ ተገለጸ።

የተሰራው ቁስ “ሄትሮዳይን ስፔክትሮ ሜትር” የሚል ስያሜ ያለው መሆኑን ከአሜሪካው የጠፈር ምርምር ናሳ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

መሳሪያው ከፍተኛ የሆነ ጨረር በመልቀቅ በጨረቃ ላይ ያሉትን የውሃ አካላት ለማጉላት እና ለመለየት ብሎም በትክክል ቦታውን ለማመላከት ያስችላልም ነው የተባለው።

እንደ ናሳ መረጃ ቀደም ሲል በተደረጉ ጥናቶች እና ሙከራዎች ጨረቃ ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ውሃ መኖሩ ቢረጋገጥም በትክክል መለየት ግን ሳይቻል ቆይቷል።

ናሳ ቀደም ብሎ ባበለፀጋቸው ቴክኖሎጂዎች ውሃን ፣ ነጻ ሃይድሮጅንን እና ሃይድሮክሲልን ለየብቻ መለየት እንዳልቻለም አስታውቋል።

የቁሱ ፕሮቶታይፕ የናሳ የምርምር ፕሮግራም ከሎንግዌቭ ፎቶኒክስ ጋር በመተባበር ተሰርቷልም ነው የተባለው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.