Fana: At a Speed of Life!

በሰበታ ከተማ የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰበታ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ፡፡
 
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ መነሻቸው ጋምቤላ ከተማ መሆኑን በሰበታ ፖሊስ መምሪያ የአካባቢ ደህንነት መረጋገጥ ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል ሃይለማርያም ተናግረዋል፡፡
 
የተያዙት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችም 35 ታጣፊ ክላሽ፣ 10 ባለሰደፍ ክላሽ፣ 46 የክላሽ ካርታ፣ 3 የተለያዩ ሽጉጦች እንዲሁም 432 የስታር፣ የኮልትና የቱርክ ሽጉጥ ጥይቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
ህግ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያጓጉዙ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ከሰበታ ከተማ ከሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.