አቶ ኦርዲን በድሪ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በክልሉ ከሚገኙ አመራሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በክልሉ ከሚገኙ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ ኦርዲን በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ በሁሉም ወረዳ መስተዳድሮች የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል፡፡
በቀጣይም በወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ፣ በሰላም፣ በሕግ የበላይነት እና የገበያ ማረጋጋት ሥራ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ሕገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራን ከመከላከል አኳያም የተጀመረው ቅንጅታዊ አሠራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡