Fana: At a Speed of Life!

በ17ኛው የዓለም አቀፍ ኢንተርኔት አስተዳደር ዝግጅት ሂደት ላይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የዓለም አቀፍ ኢንተርኔት አስተዳደር ዝግጅት ሂደትን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ÷ ኢትዮጵያ 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በ2022 እንድታስተናግድ መመረጧን አስታውሰዋል፡፡

ጉባኤው ከኢንተርኔት እድገት ጋር የተያያዙ አንገብጋቢ ጉዳዮችን፣ ኢንተርኔት አስተዳደርና ሌሎች በኢንተርኔትና ከዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጋር የተገናኙ በኢንተርኔት አስተዳደር ላይ በሚነሱ ሐሳቦች ዙሪያ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ከተለያዩ የዓለም ክፍል የሚመጡ የግሉ ዘርፍ፣ መንግስትና የዘርፉ ፖሊሲ አውጪዎች ይሳተፋሉ ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉባኤውን የዝግጅት ሂደት አስመልክቶ የተሠሩ ሥራዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በቀጣይ በትኩረት የሚተገበሩ ተቋማዊ ሥራዎችን አስመልክቶ የሥራ መመሪያና የአፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በውይይቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከጉሙሩክ ኮሚሽን፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.