የጋምቤላ ክልል ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል መንግስት ባካሄደው አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡
አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባው በሶስት አጀንዳዎች ዙሪያም ተወያይቷል፡፡
በክልሉ አደጋ ስጋት አመራር አገልግሎት በቀረበው በጎርፍ ለተጎዱ ስምንት ወረዳዎች ከ75 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች አስቸኳይ እርዳታ ለማድረግ 10 ሚሊየን ብር አጽድቋል።
የጎርፍ አደጋው ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፥ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም የተሻሻለው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መዋቅራዊ አደረጃጀት በተመለከተ ተወያይቶ አዲስ አደረጃጀት እንዲሰራ ውሳኔ አሳልፏል።
የጋምቤላ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተወሰኑ ዘርፎች በዲግሪ ደረጃ እንዲሰጥ የቀረበው ውሳኔ ሀሳብና ጥያቄ ዙሪያ ተወያይቶ በተወሰኑ ዲፓርትመንቶች ኮሌጁ ስራውን እንዲጀምር መወሰኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!