ስፓርት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያን 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ

By Alemayehu Geremew

August 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በሦስተኛነት አጠናቀቀ።

በማጣሪያው ላይ ኢትዮጵያን የወከለው ንግድ ባንክ ዛሬ በአዛም ኮምፕሌክስ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የርዋንዳውን ኤ ኤስ ኪጋሊን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

አረጋሽ ካልሳ፣ ሀሳቤ ሙሶ እና ሎዛ አበራ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የርዋንዳው ክለብ ጎል ሀሳቤ ሙሶ በራሷ ግብ ላይ አስቆጥራለች።

የውድድሩ አሸናፊ ሴካፋን ወክሎ በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ይሳተፋል።

ሁለተኛው የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ በሞሮኮ አስተናጋጅነት በጥር ወር 2015 ዓ.ም ይካሄዳል።