Fana: At a Speed of Life!

በአዊና መተከል ዞኖች አዋሳኝ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች መካከል እርቀ ሰላም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዊና መተከል ዞኖች አዋሳኝ ወረዳዎች በሚኖሩ ህዝቦች መካከል የሚፈጠሩ የግጭት መንስኤዎችን በዘላቂነት ለማስወገድ የእርቀ ሰላም ስነ ስርዓት ተካሄደ።
 
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ÷ የሁለቱ ዞን ህዝቦች የጋራ ባህል፣ወግና የቆየ አብሮነት ያልተዋጠላቸው ቡድኖች የሚፈጥሩቱን የተሳሳተ አጀንዳ በመገንዘብ በጋራ መልማት እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት አጠናክሮ በማስቀጠል የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ የሁለቱ አዋሳኝ ዞኖች አስተዳደሮች በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
 
የህዝቦችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለውን ተግባር በማጠናከር ወንጀለኞችን አጋልጦ በማውጣት በኩል ሁሉም ሚናውን መወጣት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
አቶ ጸሃይ የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት በማስቀጠል የህዝቦችን ማህበራዊና ሁሉን አቀፍ ግንኙነት በማጠናከርና በአካባቢው ያለውን ጸጋ በማልማት የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ መግለጻቸውን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.