Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከዱባይ የመጣ ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከዱባይ የመጣ ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂ ተገኘ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከተቋቋመው የሚኒስትሮች ኮሚቴ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅት በሰጡት መግለጫም በኢትዮጵያ አምስተኛው የቫይረሱ ተጠቂ መገኘቱን አስታውቀዋል።

ግለሰቡ ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ መሆኑም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ከቡርኪና ፋሶ የመጣ ጃፓናዊ የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ መሆኑ ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ተጨማሪ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.