ዓለምአቀፋዊ ዜና

አውሮፓውያን “አስከፊ ክረምቶችን” ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ተገለጸ

By Meseret Awoke

August 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አውሮፓውያን ለቀጣይ አሥር ዓመታት አስከፊ ክረምት ሊያሳልፉ ይችላሉ ሲሉ የቤልጂየም ኢነርጂ ሚኒስትር ቲን ቫን ደር ስትሬትተን ገለጹ።

ሚኒስትሩ እንዳሉት የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች አሁን ባለው የጋዝ ዋጋ ላይ ማሻያ በማድረግ በአፋጣኝ እርምጃዎችን ካልወሰዱ በቀጣዮቹ ከ5 እስከ 10 ባሉት ዓመታት “አስከፊ” የክረምት ወቅት ሊያሳልፉ ይችላሉ ብለዋል።

ይህን ችግር ለመቅረፍም የጋዝ ዋጋን መቀነስ እና ዜጎች የሚያወጡትን ወጪ መቀነስ እንደሚገባም አንስተዋል።

በጋዝ እና በኤሌክትሪክ ዋጋ ማሻሻያዎች ላይ አፋጣኝ ማሻሻያ መውሰድ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፤ የዋጋ ማሻሻያው ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ መቆጠብ እንደሚያስችል በመጥቀስ።

የህብረቱ መሪዎች የጋዝ ዋጋን ለማሻሻል የአደጋ ጊዜ ጣልቃ ገብ ስርዓትን ለመተግበር ማቀዳቸውን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።

አባል ሀገራቱ ዜጎች ለዐጋዝ እና ለኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚከፍሉትን “ከፍተኛ” ገንዘብ ለማስቀረት መስራቱ ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!