Fana: At a Speed of Life!

ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከበየዳ ወደ ሰሀላሰየምት ወረዳ በቅብብሎሽ ለሽብርተኛው ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊየን 253 ሺህ ብር መያዙን በአማራ ክልል ልዩ ኃይል የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና በህብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል፡፡
ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራትና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የበየዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.