Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ሴቶችን ማብቃት፣ መደገፍ እና ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ሴቶችን ማብቃት፣ መደገፍ እና ክትትል ማድረግ የማይቋረጥ ተግባር መሆን እንዳለበት አስገነዘቡ።

የአፍሪካ ሴቶች መሪዎች ጥምረት ስብሰባውን በአዲስ አበባ ያካሄደ ሲሆን፥ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ከጥምረቱ አባላት ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንቷ በሴቶች አመራር ሥልጠና እና ድጋፍና ክትትል በማድረግ በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ስላሉ ፕሮግራሞች ገለጻ ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የአፍሪካ ሴቶች መሪዎች ጥምረት በፈረንጆቹ 2017 በአፍሪካ ሕብረትና በተመድ የተቋቋመ ሲሆን፥ በ30 ሀገራት ብሔራዊ ቅርንጫፎች አሉት።

የኢትዮጵያ ቅርንጫፍም ከሶስት ዓመት በፊት በፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በይፋ ተቋቁሟል።

ጥምረቱ የልምድ ልውውጥ፣ የአሠራር ቅንጅት፣ ቅድሚያ ትኩረቶችን መንደፍ ላይ ትኩረቱን በማድረግ እንደሚሰራ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.