Fana: At a Speed of Life!

የተቃጣብንን የጠላት ወረራ እየመከትን የልማት ስራችንን እናስቀጥላለን- አቶ ርስቱ ይርዳ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በወላይታ ዞን በ1ሺህ ሄክታር መሬት ላይ በግል ባለሃብት እየለማ ያ የሚገኝ የበቆሎ ምርጥ ዘር ማባዥ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

አቶ ርስቱ በጉብኝት መርሐ ግብሩ ወቅት እንደገለጹት÷ በአሸባሪው ህወሓት የተቃጣብንን ወረራ በአስተማማኝ ሁኔታ እየመከትን የልማት ስራችንን እናስቀጥላለን ብለዋል።

ለክልሉ አርሶ አደሮች አስፈላጊውን የበቆሎ ምርጥ ዘር ለማቅረብ በግል ባለሃብቶች እና በሌሎች አካላት መጠነ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በባለሀብቱ እየተባዛ ያለው ምርጥ ዘር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው÷በተያዘው የምርት ዘመን ከ50 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር እንደሚያስገኝም አብራርተዋል።

በክልሉ ያለውን ጸጋ በመጠቀም በራስ ሃይል ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ከበቆሎ በተጓዳኝ በቦለቄ፣ በስንዴ እና በሌሎች ሰብሎች ምርጥ ዘር የማባዛት ስራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ወራሪው እና ሽብርተኛው ህወሓት ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገሪቱ የጀመረችው የልማት ጉዞ እንዲደናቀፍ በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም ዜጎችን ለስቃይ እየዳረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

የክልሉ ህዝብ የሽብር ቡድኑን ህወሓት እኩይ ተግባር ከማውገዝ ባለፈ ከጥምር ጦሩ ጋር የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የክልሉ ህዝብ ለጥምር ጦሩ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.