Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል-አቶ ጃንጥራር ዓባይ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ለመቀነስ የስራ እድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ፡፡

ምክትል ከንቲባው በከተማዋ ካለው ገበያ ማረጋጋትና ኑሮ ውድነት መከላከል ግብረ ኃይል ጋር የነሐሴ ወር አፈጻጸም ሪፖርትን ገምግመዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር ከበዓል በፊት የግብርና ምርቶች ላይ በቂ አቅርቦትና ተመጣጣኝ ዋጋ መኖሩን መዳሰስ እንደሚገባና የስኳርና የዘይት አቅርቦት ለህብረተሰቡ መዳረስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በከተማዋ በሚስተዋለው ህገወጥ የሲሚንቶ ዝውውር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው÷ ለበዓል በሚዘጋጁት ባዛሮችና ኤግዚቢሽኖች ላይ ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች መቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በነሐሴ ወር በእሁድ ገበያ 1 ሺህ 463 የሚሆኑ ሸማቾችን፣ከተማ ግብርና፣ኢንዱስትሪ እና ጅምላ ነጋዴዎችን በማሳተፍ በሰብል በአትክልት እና በኢንዱስትሪ ምርቶች ከ23 ነጥብ 6 ሚለየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑ ተመላክቷል፡፡

በወሩ ያለንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ 1 ሺህ 500 የንግድ ተቋማት ላይ የማስተካካያ እርምጃ መወሰዱንም ከአዲስ አበባ ስራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.