Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን ትንሣኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል አይኖርም – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ትንሣኤ ከማረጋገጥ ሊያስቆመን የሚችል አንዳች ምድራዊ ኃይል አይኖርም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የሻዴይ፣ አሸንድዬና ሶለል በዓልን ልጃገረዶች፥ ወጣቶችና ሴቶች ባከበሩበት ወቅት አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመውን ወረራ የሚያወግዝና ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ንቅናቄ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የከተማዋ ባህል ኪነጥበባትና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በንቅናቄው ላይ ታድመዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ “የዛሬውን የሻደይ፣አሸንድዬ እና ሶለል በዓል ማክበራችን ዋናው ዓላማ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ክብር ለመስጠት፣ለንፁሃን ወገኖቻችን ድምፅ ልናሰማ እና የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለማውገዝ ነው”ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ሀገርን በማስቀደም፣ በሁሉም ግንባሮች በንቃት፣ በትጋትና በአንድነት መሰለፍ ግድ ይለናልም ነው ያሉት ከንቲባዋ።

ኢትዮጵያ ለሰላም የዘረጋችው እጅ ሳይታጠፍ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያበረውን ወራሪ ኃይል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲፈጥርበትም መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ እና ለጀግባው ሠራዊቱ ያልተቆጠበ ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.