Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የከፈተውን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ በሁሉም ዘርፍ በቅንጅት መስራት ይገባል – አቶ አህመድ ሽዴ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን በብሔርና በሃይማኖት ሳንከፋፈል በአንድነት ለሀገራችን ህልውና በደጀንነት መቆም አለብን ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡
 
አቶ አህመድ ሽዴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ÷የመንግስት ሰራተኞች የዕለት ተዕለት ስራቸውን በሃላፊነት ከመተግበር ባለፈ አሸባሪው ህወሓት ለሶስተኛ ጊዜ የተከፈተውን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡
 
ለዚህም ኢትዮጵያውያን በብሔር እና በሃይማኖት ሳንከፋፈል በአንድነት ለሀገራችን ህልውና በደጀንንት መቆም አለብን ነው ያሉት፡፡
 
ዜጎች የህወሓትን ወረራ ለመመከትና በድል ለማጠናቀቅ ለመከላከያ ሰራዊት የሎጂስቲክና የስነ ልቦና ድጋፍ በመስጠት ደጀንነታቸውን አንዲያረጋጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የሚኒስቴሩ ሰራተኞች ከልማት አጋሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተጠቅመው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በወራሪው ሃይል ላይ ጫና በማሳረፍ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
 
ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው÷የህወሓትን ወረራ ቀልብሶ የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል በሚደረገው ትግል በደጀንነት ከመቆም በተጓዳኝ ባለፉት የተመዘገቡ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለማስቀጠል ሳይዘናጉ መስራት አንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.