Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት የስልጣን ቆይታ በ2 ዓመታት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት የሥልጣን ጊዜ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት እንዲራዘም መወሰኑን የሀገሪቱ የተሃድሶ ጥምር ክትትልና ቁጥጥር ኮሚሽን አስታወቀ።

ውሳኔው የተላለፈው 75 በመቶ በሚሆኑት የኮሚሽኑ አባላት መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረትም የሽግግር መንግስቱ የሥልጣን ጊዜ ምርጫ ከማካሄዱ በፊት ላልተፈቱ ጉዳዮች ዕልባት ለመሥጠት ከፈረንጆቹ የካቲት 2023 እስከ የካቲት 2025 ለሁለት ዓመታት ተራዝሟል፡፡

ኮሚሽኑ የሽግግር መንግስቱ የሥልጣን ጊዜ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት እንዲራዘም ለመወሰን የተሻሻለውን የደቡብ ሱዳን የግጭት አፈታት መርኅዎች መከተሉን ጠቁሟል፡፡

እንደ ጥምር ክትትልና ግምገማ ኮሚሽኑ ጊዜያዊ ሊቀ-መንበር ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ ÷

የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት ሥልጣን በ2 ዓመታት የማራቸዝ ሀሳብ በተሻሻለው የሀገሪቷ ሕገ መንግሥት መርሆዎች መሠረት የሽግግር ብሔራዊ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ ማፅደቅ እንደሚያስፈልግ ቻርለስ ታይ ጊቱዋይ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.