Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር፣ ደብረ ብርሃን እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው፡፡
 
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ5 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
 
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ የስልጠና መርሐ ግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
 
በተመሳሳይ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 900 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው ።
 
ተመራቂዎቹ በመደበኛ ፣ በማታና በተከታታይ ፕሮግራሞች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እንዲሁም በሶስተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
በሰላም አስመላሽ እና አበበ የሸዋልዑል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.