Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ፑቲን ያቀረቡትን የማሻሻያ እቅድ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያቀረቡትን ማሻሻያ እቅድ አፀደቀ።

በፕሬዚዳንቱ የቀረበው ማሻሻያ ፑቲን እስከ ፈረንጆቹ 2036 በስልጣን እንዲቆዩ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

ይህን ተከትሎም ፑቲን ሃገራቸውን ለሁለት የስልጣን ዘመናት መምራት የሚችሉበትን እድል አግኝተዋል።

ፑቲን ከሁለት ወር በፊት የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ እንደሚፈልጉ መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ካቢኔ መበተኑ የሚታወስ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካቢኔ መበተን ተከትሎም ሚሃይል ሚሹስቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውም አይዘነጋም።

በወቅቱ የቀረበው የፑቲን እቅድ የሩሲያን የመንግስት አስተዳደር ከፕሬዚዳንታዊ ወደ ፓርላማ የሚቀይር ነው።
የሩሲያ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ፑቲን ሩሲያን የግል ንብረታቸው አደረጓት በሚል ሲኮንኑ ይደመጣሉ።

አዲስ ያቀረቡት እቅዳቸውም ከአራት አመት በኋላ የሚያልቀውን የስልጣን ዘመን በህገ መንግስት ማሻሻያ ሰበብ በማራዘም ሩሲያን በብቸኝነት ለመምራት ያለመ ነው በሚል ተችተዋቸዋል።

ምንጭ፦ ሞስኮ ታይምስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.