Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የመኸር እርሻ ስራን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ መልጋ ወረዳ በ35 ሄክታር ማሳ ላይ በኩታ ገጠም የለማ የገብስ ማሳን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተዳደሩ በልማቱ የተሳተፉ አርሶ አደሮችን በማወያየት አበረታተዋል።
የመኸር እርሻ እንቅስቃሴው በዝናብ እጥረት የተስተጓጎለውን የበልግ አዝመራ ምርትን ለማካካስ በሚያስችል መንገድ መልማቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
ልማቱን ለማጠናከር ያግዛል ለተባለው ዘር መግዣ የክልሉ መንግስት 47 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.