Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከክልሉ ሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ፣ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በክልሉ ከሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጃፈር ሱፊያን÷አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት መክፈቱን አስታውሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት የሠላም አማራጭን የተከተለው የትግራይን ህዝብ ዘላቂ ጥቅም በማሰብ እንደሆነ ጠቁመው ቡድኑ ግን ለሶስተኛ ጊዜ ወረራ መፈጸሙን ተናግረዋል።

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በብሄር፣ በሀይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይከፋፈል በአንድነት በመቆም መንግስት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅበት ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ የተገኙት የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ÷ የኢፌዴሪ መንግስት የሰጠውን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው አሸባሪው ህወሓት በሀገሪቱ ላይ የከፈተውን ጦርነት አውግዘዋል።

የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በሚከናወኑ ተግባራት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀው ህዝቡም አንድነቱን በማጠናከርና የአካባቢውን ሰላም በንቃት መጠበቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

በተለይም የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እየተዋደቀ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላትን የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ማንሳታቸውን ከሀረሪ ከልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.