ጃክ ማ ለአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚረዳ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ሊያደርጉ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሊ ባባ መስራች እና ባለቤት ጃክ ማ የአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚያደርጉት ጥረት የሚውል ድጋፍ ሊያደርጉ ነው።
ድጋፉ ለ54 የአፍሪካ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል ለሚያደርጉት ጥረት የሚውል የህክምና ቁሳቁስ መሆኑንም ጃክ ማ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
በዚህ መሰረት ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሃገር ቫይረሱን ለመለየት የሚረዱ 20 ሺህ መመርመሪያዎች፣ 100 ሺህ የፊት ጭምብል፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው 1 ሺህ መከላከያ ልብሶች የሚከፋፈል ይሆናል።
ድጋፉም በኢትዮጵያ አማካኝነት ለሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ይዳረሳል ነው የተባለው።