Fana: At a Speed of Life!

የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ባንኮች ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥል- አቤ ሳኖ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት የማድረግ ውሳኔ የኢትዮጵያ ባንኮች በትብብር ብቁ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥል ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናገሩ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ13ኛ መደበኛ ስብሰባው የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ የቀረበው ረቂቅ ፖሊሲ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ውሳኔውን አስመልክቶ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ የባንኩ ዘርፍ ለዓለም ገበያ ዝግ ሆኖ መቆየቱ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ዕድገት አቀጭጯል፡፡

የባንክ አገልግሎቱን ቀስ በቀስ ለዓለም አቀፍ ውድድር ክፍት በማድረግ የሀገር ውስጥ ባንኮች የውድድር አቅማቸውን እያጎለበቱ እንዲሄዱ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ ዓለም አቀፍ ልምዶችን ለመቅሰም ዕድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል፡፡

የባንኩ ዘርፍ ለዓለም ገበያ ክፍት መደረጉ የሚበረታታ ቢሆንም በጥንቃቄ መመራት እንዳለበትም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በውድድሩ የሀገር ውስጥ ባንኮች እንዳይጎዱ በተወሰነ የአክሲዮን ድርሻ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ በማድረግ በሂደት የአክሲዮን መጠናቸውን እያሳደጉ የሚሄዱበትን አሠራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.