የሀገር ውስጥ ዜና

በናይል ወንዝ ውሃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

September 05, 2022

አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይል ወንዝ ውሃ ፍትሐዊ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የተፋሰሱ ሀገራት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የተፋሰሱ ሀገራትና የቀጣናው የዘርፉ ተቋማት ተወካዮች፣ በተፋሰሱ ሀገራት የሚገኙ ከሰባት በላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና የናይል ጉዳይ ተመራማሪዎች ተገኝተዋል።