Fana: At a Speed of Life!

ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
 
ኮሚሽኑ ከነሐሴ 20 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 73 ነጥብ 4 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ እና 7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የወጪ ኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡
 
ከተያዙት እቃዎች ውስጥም አልባሳት፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሃኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
 
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በብረበራና በጥቆማ የተያዙ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘባ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.