የኬንያ ፍርድ ቤት የራይላ ኦዲንጋን ክስ ውድቅ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተሸንፈው የነበሩት እና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የወሰዱት ራይላ ኢዲንጋ ያቀረቡትን ክስ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
በዚህም መሰረት ቀደም ብሎ በሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አሸናፊ የተባሉት ዊሊያም ሩቶ የሀገሪቱ ተመራጭ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተረጋግጧል።
ዊሊያም ሩቶ ከሶስት ሳምንት በፊት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 5ኛው የኬንያ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
ከ14 ሚሊየን በላይ ኬንያውያን ድምጽ ሰጥተውበታል በተባለው ምርጫ ዊሊያም ሩቶ 50 ነጥብ 49 በመቶ ድምጽ በማግኘት ነበር ያሸነፉት።
ተፎካካሪያቸው የነበሩት ራይላ ኦዲንጋም የምርጫ ውጤቱን አልቀበልም በማለት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የኦዲንጋን ክስ ውድቅ አድርጎታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!