Fana: At a Speed of Life!

ባራክ ኦባማ የ“ኤሚ`ን አዋርድ” አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)44ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቴሌቪዥኑ ዘርፍ ተሳትፏቸው ባሳዩት ልኅቀት የ “ኤሚ`ን አዋርድ” አሸናፊ ሆኑ፡፡

ባራክ ኦባማ ሽልማቱን ያገኙት በኔትፍሊክስ ዘጋቢ ፊልም ላይ ባሳዩት “አስደናቂ” አተራረክ ነው ተብሏል፡፡

አሸናፊ ያደረጋቸው የኔትፍሊክስ ዘጋቢ ፊልም “አወር ግሬት ናሽናል ፓርክስ” በሚል ርዕስ በአምሥት ክፍሎች የተዘጋጀው መሆኑም ተነግሯል፡፡

ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ “ሀየር ግራውንድ” የተሰኘው ፕሮዳክሽን ኩባንያ ባለቤት ናቸው፡፡

ሽልማቱን ያስገኘላቸው ዘጋቢ ፊልምም በዚሁ በግል ኩባንያቸው የተዘጋጀ መሆኑን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡

“ኤሚ አዋርድ” በተለያዩ የቴሌቪዥን እና ታዳጊ ሚዲያ ዘርፎች የላቀ ብቃት ላሳዩ አካላት የሚሰጥ ታላቅ ሽልማት ወይም እውቅና ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.