Fana: At a Speed of Life!

የዩሮ ምንዛሬ  በ20 ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ  ማሽቆልቆሉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት የጋራ መገበያያ  የሆነው ዩሮ በ20 ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ0 ነጥብ 99 ዶላር በታች መውረዱ ተገለጸ።

በአውሮፓ ገበያ፥  የዩሮ ዋጋ በ 0 ነጥብ 7 በመቶ ወይም ወደ 0 ነጥብ 9880 ዝቅ ያለ ሲሆን፥ ይህም ከፈረንጆቹ 2002 ጀምሮ በጣም የወረደ ነው ተብሏል።

በአውስትራሊያ ብሔራዊ  ባንክ የምንዛሪ ስትራቴጂ ባለሙያ የሆኑት ሮድሪጎ ካትሪል “ሚንት” ለተሰኘው የህንድ የፋይናንሺያል ጋዜጣ  በሰጡት አስተያየት፥  “ዩሮ የሩሲያ የጋዝ  አቅርቦት መቋረጥን ተከትሎ ገና የበለጠ አሉታዊ ተፅእኖ ውስጥ ይወድቃል ያሉ ሲሆን፤ ጋዝ የለም ማለት ምንም እድገት የለም ማለት ነው” ሲሉም አክለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ዩሮ በ1 ነጥብ 02 ዶላር ይመነዘራል ብለው ተንብየው የነበሩት የጎልድማን ሳችስ ተንታኞች በበኩላቸው፥  የዩሮ ምንዛሬ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ከ0 ነጥብ 99 ዶላር ወደ 0 ነጥብ 97 ይቀንሳል በማለት ትንበያቸውን አስቀምጠዋል።

ተንታኞቹ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥም ዩሮ ከዶላር ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ እንደሚሆንም ነው የተናገሩት።

የሩስያ  ኃይል አቅራቢ ተቋም ጋዝፕሮም በደረሰበት የተርባይን ብልሸት ምክንያት የተፈጥሮ ጋዝ ከሩስያ ወደ ጀርመንና አውሮፓ የሚተላለፍበት መስመር (ኖርድ ስትሪም 1)  እንደማይጀምር መናገሩ ይታወሳል።

በርካታ የጋዝ ተርባይኖች በመዘጋታቸው ኖርድ ስትሪም 1 ከሰኔ ጀምሮ በዝቅተኛ አቅም ሲሰራ የቆየ ሲሆን ለአቅርቦቱ መቀነስም በምዕራቡ ዓለም ማዕቀብ ምክንያት የጥገና መሳሪያዎች እንዲዘገዩ በማድረጉ ነው ሲል ጋዝፕሮም መግልጹን የአርቲ ዘገባ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.