Fana: At a Speed of Life!

ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ “ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንንና ጉልበታችንን እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከማዋል በላይ ሀገርን የመውደድ መገለጫ የለም” ብለዋል።

ከለውጡ ወዲህ በማኅበራዊ ኃላፊነት ማኅበራዊ ችግርን የመፍታት መርሕ መተግበሩን አንስተዋል።

በዚህም ማዕድ ማጋራት፣ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ቤት መሥራት፣ ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን መገንባት፣ የተቸገሩ አርሶ አደሮችን ማሳ ማረስ እና አካባቢን አረንጓዴ ማድረግ ባህል እንዲሆኑ መሰራቱንም አስታውሰዋል።

ሚሊየኖችም የዚህ ተሳታፊ ሆነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከሕጻናት እስከ አረጋውያን ባህላቸው እንዳደረጉትም አስታውቀዋል።

አያይዘውም በዚህ ዓመት በተደረጉ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ለተሳተፉ ሁሉ በራሳቸውና በመንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

አገልግሎቱን ያገኙት ወገኖች እንደሚመርቁንና እንደሚጸልዩለን አምናለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ኢትዮጵያችን በእነዚህ ወገኖች ምርቃትና ጸሎት ፈተናዎቿን አሸንፋ እንደምትጓዝ እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.