Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ 100 ሺህ ሔክታር በሩዝ ምርት ተሸፍኗል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በክረምት እርሻ 100 ሺህ ሔክታር በሩዝ ምርት መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ጌቱ ገመቹ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዘንድሮው የክረምት እርሻ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታር በተለያየ ሰብል ተሸፍኗል፡፡

በዚህም ከውጭ ሀገራት የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ይህን ለማሳካትም 100 ሺህ ሔክታር በሩዝ መሸፈኑን ገልጸው÷ ከዚህም 4 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

እንደ ኦሮሚያ ክልል ከሩዝ በተጨማሪ የስንዴ ልማት በከፍተኛ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው÷ በበጋ መስኖ 669 ሺህ ሔክታር መሬት በስንዴ ተሸፍኖ 19 ሚሊየን ኩንታል ምርት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ክረምትም በክልሉ በ1 ነጥብ 7 ሔክታር ላይ ስንዴ እየለማ መሆኑን ጠቁመው÷ ከዚህም 61 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በክልሉ በክረምት እርሻ በተለያየ ሰብል ከተሸፈነው 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሔክታር ውስጥ 75 በመቶው ወይም 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ሔክታሩ በኩታ ገጠም እየለማ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.