Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የደረሰብን ምት  የምንቋቋመው አይደለም – የአሸባሪው ህወሓት ምርኮኞች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የደረሰብን ምት  የምንቋቋመው አይደለም ሲሉ በሰቆጣ ግምባር እጃቸውን የሠጡ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡

ምርኮኞቹ  እየተካሄደ ባለው ጦርነት አማራን መደምሰስ አለባችሁ የሚል ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል ውስጥ ከፍተኛ አፈና እና የመብት ጥሰት እየተፈፀመ መሆኑን የገለፁት ምርኮኞቹ  ቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰውን ወከባ እና እንግልት ላለማየት የሽብር ቡድኑን መቀላቀላቸውን ገልፀዋል፡፡

የጦርነት ፍላጎት ባይኖራቸውም  ከሚሰሩበት ቦታ በሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ተገደው ወደ ማሰልጠኛ እንደተወሰዱም አብራርተዋል።

በውጊያውም በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የደረሰብንን ምት ፈጽሞ የምንቋቋመው አልሆነም ያሉት ምርኮኞቹ ብዙዎች አጠገባችን ተደምስሰውብናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በግንባሩ የተሰለፉ የሽብር ቡድኑ አመራሮች ሞተዋል፣ የተረፉት ደግሞ  ጥለው ሸሽተዋል ሲሉ ምርኮኞች መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.