Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ የሙከራ ክትባት በሰዎች ላይ ተደረገ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 8፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያስችል የሙከራ ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዎች ላይ  መሞከሩ ተሰማ፡፡

ክትባቱ የተሞከረው በዋሽንግተን ሲያትል በሚገኘው የኪያሰር ፐርማነንቴ  የምርምር ተቋም ውስጥ በአራት  በጎ ፈቃደኛ  ሰዎች  ላይ ነው ተብሏል፡፡

የመጀመሪያውን ክትባት የወሰደችው የ43 ዓመቷ ጀኔፈር የሁለት ልጆች እናት መሆኗም ተነግሯል።

ክትባቱ ለበሽታው መነሻ ከሆነው ቫይረስ የዘር ውርስ የተወሰደ ሲሆን ÷ ምንም አይነት ጉዳት የሌለው ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ክትባት ጨምሮ ሌሎች በምርምር ላይ ያሉ  መድኃኒቶችም  ውጤታማ መሆናቸወን ለማወቅ ወራትን  እንደሚወስድ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በዓለም ዙሪያ ያሉ ሳይንቲስቶች  ለወረርሽኙ መድሀኒት ለማግኘት ፈጣን የሆኑ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.