በአፍሪካ የአየር ንብረት ማላመድ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚመጣ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የአፍሪካ የማላመድ ማፋጠን ፕሮግራም “ በአፍሪካ የአየር ንብረት ማላመድ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ሲሉ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ገለፁ፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በሆላንድ ሮተርዳም በተካሄደው የአፍሪካ የማላመድ ማዕከል ጉባኤ (African Adaption Summit) ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም÷ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የምግብ ዋስትና፣ የእንስሳት እርባታና የአርብቶ አደር ገቢዎች ላይ ያለው ከፍተኛ ተጽዕኖ፣ ውሃ ፍለጋ የህዝብ መፈናቀልን እያስከተለ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
“ይሁንና በእነዚህ ችግሮች መሀል ተስፋ አለ” ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ በስንዴ ምርት ላይ ትልቅ ለውጥ እያስመዘገበች እንደሆነ እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ መርሕ ገብር በርካታ የችግኝ ማፊያዎች እንዲቋቋሙና ቢሊየን ችግኞች በዓመት ለማልማት መቻሏን ገልፀዋል።
“የአፍሪካ የማላመድ ማፋጠን ፕሮግራም (African Adaptation Acceleration Program) በአፍሪካ የአየር ንብረት ማላመድ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ገልፀዋል፡፡
ለዚህ ፕሮግራም ሁሉም የልማት አጋሮች የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን÷ይህን በማድረግ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እንደምትችል እናረጋግጣለን” ሲሉ መናገራቸውን ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!