Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በእንስሳት ላይ ግፍና በደል እየፈጸመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ ጋዝጊብላ ወረዳ ዛሮታ ቀበሌ የአርሶ አደር ንብረት እንስሳቶችን በመግደልና በመዝረፍ ዋነኛ የህዝብ ጠላት መሆኑን አሳይቷል።

በወራሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች፥ “አርሰን፣ አምርተን ልጅ እናሳድግበታለን ፤ ከእርሻ በተጨማሪ ህይወታችን እንመራበታለን ፤ እንገለገልባቸዋለን ብለው የምንተማመንባቸውን በሬ፣ ፍየልና በግ እንዲሁም ዶሮ በአሸባሪ ቡድኑ ተገድለውብናል” ብለዋል።

የቻለውን በልቶ እንስሳቱን በግፍ በመግደል ከጥቅም ውጭ በማድረግ የአርሶ አደሩን ቅስም መስበሩን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንስሳት በመዝረፍና መግደል ቡድኑ ለአርሶ አደሩ ያለውን ከፍተኛ ጥላቻ ያሳየበት ሰይጣናዊ ድርጊት እንደሆነም ተጓጂዎች አስረድተዋል።

የወራሪው ህወሓት ዋነኛ ዓላማው አርሶ አደሩ እንዳያርስ፣ እንዳያመርት በማድረግ ህዝቡን ለችግር፣ ርሀብ፣ ስቃይና መከራ መዳረግና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን መጉዳት መሆኑንም ይናገራሉ።

ወራሪው ቡድን ‘‘ከህዝብ ጋር ፀብ የለኝም፣ ጠላቴ የአማራ አመራር ነው’’ እያለ በአፈ ቀላጤዎቹና ሚዲያዎቹ የሚለፍፈው ፍፁም ሀሰት መሆኑን በጭካኔ ተግባሩ ማስመስከሩም ነው የተገለጸው።

አሸባሪው በክፋት ተወልዶ በክፋት ያደገ በክፋቱም ወደ መቃብር እየወረደ ያለ ዓላማ ቢስ ቡድን እንደሆነ አውቆ የሚሰጠውን የውሸትና የመከፋፈያ ሃሳብ ወደ ጎን ብሎ በአንድነትና በቁርጠኝነት መታገል ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል ተጓጂዎቹ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.