ከዓባይ ተፋስስ ሀገራት የተውጣጡ አባላት ያሉት ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የዓባይ ተፋስስ ሀገራት የተውጣጡ አባላት ያሉት ልዑክ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ጎበኘ።
ልዑኩ በምርምር ተቋማት የሚሰሩ የውሃ ሃብት ምሁራን፣ በየአገራቱ የቀድሞ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የሚዲያ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከትናንት በስቲያ በአዲስ አበባ በተጀመረው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ምክንያታዊና ፍትሐዊ የውሃ ሃብት አጠቃቅም ላይ የሚመክረው ቀጠና አቀፍ የዓባይ ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጡ ናቸው።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የኢትዮጵያ ምሁራንም በጉብኝቱ መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!