Fana: At a Speed of Life!

የራስ ምታት መንስኤና መፍትሄዎቹ

 

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የራስ ምታት በየትኛውም የጭንቅላት /የራስ ክፍል/አካባቢ የሚከሰት የህመም አይነት ነው፡፡

ህመሙ የሚሰማዎት ጭንቅላትዎን ከፍሎ በአንዱ በኩል አሊያም በሁለቱም በኩል ሊሆን እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ ፥ ህመሙ የመውጋት ወይም ለመግለፅ የሚያስቸግር አይነት ስሜት ሊኖረው ይችላል።

የራስምታት ቀስበቀስ ወይም በድንገት ሊመጣ የሚችል ሲሆን ፥ ህመሙ ከጀመረ በኋላ ለሰዓታት ወይም ለቀናት ሊቀጥል ይችላል።

የራስ ምታት በአብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ቀላል በሆኑ ምክንያቶች ሲሆን ፥ አንዳንድ ጊዜ ግን ለህይወት አስጊ በሆኑ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል።

በዚህም ሌላ ምክንያት የሌለው የራስምታት አይነት እና ምክንያት ያለው ራስ ምታት በመባል በሁለት ይከፈላሉ፡፡

1.ፕራይመሪ የራስ ምታት (ሌላ ምክንያት የሌለው የራስምታት አይነት)

ይህ የራስምታት አይነት የሚከሰተው በጭንቅላትዎ ውስጥ ያሉና ህመም እንዲሰማዎ የሚያደርጉ ክፍሎች ችግር ሲከሰትባቸው ወይም ከመጠን ያለፈ ስሜት በሚፈጠርበት ወቅት ነው።

በጣም ከሚታወቁትና ከዚህ የራስምታት አይነት ውስጥ የሚመደቡ የራስ ምታት አይነቶች  መካከል:-  ክላስተር ሄድኤክ ፣ማይግሬይን ሄድኤክ ፣ቴንሽን ሄድአክና የመሳሰሉት ሲሆኑእነዚህ የራስ ምታት አይነቶች የተወሰኑ የአኗኗር ዘይቤ ምክንቶች ሊያስነሱትና ሊያባብሱት ይችላሉ።

2.ሰከንደሪ ራስምታት (ምክንያት ያለው)

ይህ የራስምታት አይነት ሌላ ህመም ሊያመጣው  የሚችል  የመሰረታዊ ህመም ምልክት ሲሆን ለዚህ የራስ ህመም አይነት ምክኒያት ከሚሆኑ ህመሞች መካከል:-ድንገተኛ የሳይነስ ኢንፌክሽን ፣በጭንቅላት ውስጥ በደም መልስ ውስጥ ደም መርጋት ፣ በጭንቅላት ውስጥ የደም ቧንቧ መወጠር፤ መስፋት መከሰት ፣የጭንቅላት ውስጥ ዕጢ፣ በካርቦንሞኖኦክሳይድ መመረዝ፡- ለምሳሌ የከሰል ጭስ፣ የፈሳሽ ዕጥረት(ዲሃይድሬሽን) ፣የጥርስ ችግር ፣ የጆሮ ኢንፌክሽን ወዘተ…. ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የህክምና ባለሙያ ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?

እራስን መሳት ከተከሰተ፣የመቀበጣጠር ወይም የሰዎችን ንግግር መረዳት ያለመቻል ከተከሰተ፣ ከፍተኛ ትኩሳት ካለብዎ(ከ39° ሴ. ግሬድ በላይ )፣ባንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍልዎ የመደንዘዝ፣ የመስነፍ እና ያለመታዘዝ ምልክት ካለ፣የአንገት ያለመታጠፍ ችግር ካለ፣  የዕይታ ችግር ከገጠመዎ ፣የመናገር ችግር ከገጠመዎ ፣ የመራመድ ችግር ከገጠመዎ ፣ማቅለሽለሽና ትውከት የመሳሰሉት ከተከሰቱ የህክምና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል፡፡

ለራስ ምታት ሊሰጡ የሚችሉ ህክምናዎች (ለማይግሬይን አይነት የራስ ምታት ህመሙን ሊያስታግሱ የሚችሉ መድሃኒቶች)

 • ዕረፍት ማድረግ (ጨለማ ክፍል ውስጥ ቢሆን ይመረጣል )
 • አስፒሪን፣አይቡፕሮፌንና አሴታሚኖፌን የመሳሰሉት መለስተኛ የማይግሬይን ህመምን ሊያስታግሱ ይችላሉ
 • እንደ ትሪፕታነስ፣ኢርጎትስ፣ኦፕዮይድስ፣የትውከት ማስታገሻ እንክብሎችና ጉሉኮኮርቲኮይድስ የመሳሰሉት መድሃኒቶችም መውሰድ

የማይግሬይን ራስምታትን ለመከላከል የሚሰጡ ህክምናዎች

 • ካርዲዮቫስኩላር ድረግስ( ሮፕራኖሎል፣ ሜቶፕሮል )
 • አንታይዲፕሬሳንት(አሚትሪፕትሊን )
 • ለሚጥል ህመም ሊሰጡ ከሚችሉ መድሃኒቶች እንደ ቫልፑሬት ሶዲያም ያሉት ይገኛሉ።
 • የአኗኗር ዘይቤ ለውጥና የቤት ውስጥ ህክምና
 • ለራስዎ የሚያደርጉት እንክብካቤ የራስ ምታትን የህመም ስሜትዎን ሊቀንስ ይችላል።
 • የጡንቻ ማፍታታት እንቅስቃሴ ማድረግ
 • ዮጋና ሜድቴሽን የመሳሰሉት ናቸው።
 • በቂ እንቅልፍ ማግኘት ፡- በእያንዳንዱ ሌሊት በቂ እንቅልፍ ለማግኘት መቻል ነው እንጂ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ መተኛት የለብዎትም፤ ሁሌም ቢሆን ወደ አልጋ ለእንቅልፍ የሚሄዱበትና ሲነጋ የሚነሱበት ሰዓት ተመሳሳይ ቢሆን ይመረጣል
 • እረፍት ማድረግና ዘና ማለት ፡- ያለዎት ራስምታት ማይግሬይን ከሆነ ከተቻለ ፀጥ ያለና ጨለማ ክፍል ቢያርፉ ይመረጣል፤በረዶ በጨርቅ አድርገው በማጅራትዎ ስር ያድርጉና በመጠኑ ህመም በሚሰማዎ የጭንቅላትዎ አካባቢ ጫን ጫን ያድርጉ::
 • ሁሌ የራስምታት ደያሪ መያዝ/መመዝገብ፡- ይህን አዘውትሮ ማድረግ የራስምታት ህመምዎን ምን እንደሚያስነሳብዎና የትኛው ህክምና እንደሚያሽልዎ ለማወቅ ይረዳል።

ምንጭ :-ኸልዝ ላየን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.