አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመደቡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸው ተገለፀ።
የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አወሉ አብዲ እና የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫውም አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ምደባ መካሄዱንም ነው የገለፁት።
በቀጣይም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዞኖች እና ወረዳዎች እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።
ትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል በመግለጫው ላይ ፥ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግና የትግራይ ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል እንደሚሰራ ሀልፀዋል።
በተጨማሪም በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ በስፋት መሳተፍና ማሸነፍ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አመልክተዋል።
በሀይለኢየሱስ ስዩም