የአፍሪካ 2022 የቴክኖሎጂ ኤክስፖ መርሐ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ 2022 የቴክኖሎጂ ኤክስፖ እና “የኤን ቲ ኤፍ 5″(NTF 5) ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ ኤክስፖው ትልልቅ ኩባንያዎች፣ የፈጠራ ባለተሰጥኦዎች፣ በአይሲቲ ዘርፍ የተመረጡ ቴክኖሎጂዎች፣ የሮቦት፣ ስታርታፖችን፣ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ማቀድ የሚያስችሉ አሠራሮችን ማሳየት የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን በአንድ ላይ ያገናኘ ነው፡፡
ጠቀሜታውም የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የዘርፉ የመንግሥትና የግሉ ተዋንያን የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አካላት የተገናኙበትን መድረክ÷ ለትውውቅ፣ ለትስስር እና ለልምድ ልውውጥ እንዲጠቀሙበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
“የ NTF V 5” የኢትዮጵያ ፕሮጀክትም በዲጂታል ዘርፉ ዘላቂ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የመካከለኛና አነስተኛ የቴክኖሎጂ እና የግብርና ኢንተርፕራይዞችን እንዲተሳሰሩ ብሎም እንዲቀራረቡ ዕድል ይፈጥራል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ከተለዩ እና ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች ግብርና አንዱ መሆኑን ጠቁመው÷ የግብርናን ዘርፍ በዲጂታል ቴክኖሎጂ መደገፍ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡
ለፕሮጀክቱ ስኬት እና ለጋራ ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ሚኒስቴሩ ግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!