Fana: At a Speed of Life!

ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአስር ዓመታት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ኢትዮጵያ በጣሊያን ጦር በግፍ በተወረረችበት ወቅት ለአራት ዓመታት ያህል ከሌሎች ሀገር ወዳድ ጀግኖች ጋር በአርበኝነት ታግለዋል።

አርበኛ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ፥ ሀገር ከጣሊያን ወረራ ነጻ ከወጣች በኋላም በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ተመድበው ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በቅንነት አገልግለዋል።

ሀገር ወዳዱ አርበኛ ሊቀ ትጉሃን፥ አስታራቂ ሽማግሌ ሆነው በተመረጡበት ሁሉ በእድሜያቸው ባካበቱት ጥበብና ቅን ልቦና ሀገራቸውን በትጋት ያገለገሉ የሕዝብ ባለውለታ ነበሩ።

ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ ባደረባቸው ህመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጳጉሜን 2 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነ-ስርዓታቸው ጳጉሜን 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለአርበኞች በተፈቀደው ቦታ እንደሚፈጸም የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.