የካፋ እና የከምባታ ጠምባሮ ዞኖች ለሰራዊቱ ሃብት እያሰባሰቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ እና የከምባታ ጠምባሮ ዞኖች አሸባሪው ህወሓት ለ3ኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስና በድል ለማጠናቀቅ ለመከላከያ ሠራዊት ሃብት እያሰባሰቡ ነው፡፡
ዛሬ በካፋ ዞን “እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ” በሚል መሪቃል ለመከላከያ ሠራዊት በተደረገ የድጋፍ ንቅናቄ ከሁሉም ወረዳዎች 139 ሰንጋ በሬ እና 26 በግ መሰብሰብ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ከ13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 105 ሰንጋዎች፣ 250 በጎችና ፍየሎች እንዲሁም ከ600 ኩንታል በላይ የማይበላሹ ምግቦች እና 60 ኩንታል ስኳር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
አሸባሪው ህወሓት የጀመረውን ጦርነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀልበስ ሁሉም ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ ሕዝባዊ ደጀንነቱን በተግባር ማሳየት አለበት መባሉን ከዞኖቹ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ ሁሉም ዜጋ አንድነቱን በማጠናከር የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!